ገደቡ ካልተነሳ የበጀት ድጎማውን እንደማይለቅ የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ
የአውሮፓ ኅብረት የሰብዓዊ ዕርዳታ የሚያቀርቡ ድርጅቶች በትግራይ ክልል ያለ ገደብ እንዲንቀሳቀሱ እስካልተፈቀደ ድረስ፣ ለኢትዮጵያ ያፀደቀው የበጀት ድጎማ እንደማይለቀቅ አስታወቀ።
የኅብረቱ ምክትል ኮሚሽነርና የውጭ ጉዳይና ደኅንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፍ ቦሬል በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ቀውስ መባባስ የአውሮፓ ኅብረትን በእጅጉ እንደሚያሳስበው፣ በዚህ ጉዳይ ላይም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በስልክ መወያየታቸውን ገልጸዋል።
በውይይታቸው ወቅትም በትግራይ ክልል ያለው ሰብዓዊ ቀውስ ኅብረቱን እንደሚያሳስበው ለአቶ ደመቀ እንደገለጹላቸው የጠቆሙት ኃላፊው፣ ሰብዓዊ ዕርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች በትግራይ ክልል ያለ ምንም ገደብ እንዲንቀሳቀሱ ሊፈቀድ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ዓርብ ጥር 7 ቀን 2013 ዓ.ም. አስታውቀዋል።
‹‹ይህ የአውሮፓ ኅብረት ጥያቄ አይደለም፡፡ ይህ በዓለም አቀፍ ሕግ የተደነገገ የመንግሥታት ግዴታ ነው፤›› ሲሉም በትዊተር ገጻቸው አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ መንግሰት የኢንተርኔት አፈናውን አጠናክሮ መቀጠሉን ፍሪደም ሀውስ አስታወቀ
በኢትዮጵያ በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የሚፈጸመው አፈና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን ፍሪደም ሀውስ የተሰኘው ዓለም ዓቀፍ የሰው ልጆች መብት ተከራካሪ ቡድን አስታወቀ፡፡ መንግስት በሀገር...
አሜሪካ የኤርትራ ሠራዊት ከኢትዮጵያ እንዲወጣ ግፊት አደርጋለሁ አለች
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአሜሪካ መንግሥት ወኪል ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ የአፍሪካን ቀጣናዊ ሰላም በሚመለከት ማክሰኞ ግንቦት 10 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣...
ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቃሉ አማራዎች እና የህገመንግስቱ አንድምታ
(ዘላለም እሼቱ)
በሀገሪቱ የመዘዋወር መብት እንዲሁም ቋሚ የመኖሪያ ቦታ የመመስረት ለሁሉም ዜጎች በዘር በሀይማኖት በብሔር ልዩነት ሳይደረግ የተሰጠ ሰፊ መብት መሆኑን ከህገመንግስቱ አንቀፅ 32 ላይ...
ደሴ እና የሸዋበር መስጊድ! የጢጣው ኮሌኔል ጉድ!
(በውብሸት ሙላት) እስከ 2003/4 ዓ.ም. (በትክክል ባላስታውሰውም) ድረስ ዋና ተልእኮው ግጭት መፍጠር የሚመስል ተግባር ውስጥ የተሰማራ አንድ ኮሌኔል(ስሙን ላለመጥቀስ ነው) ነበር፡፡ ጢጣ የወታደር ካምፕ...
ኢትዮጵያ በትግራይ መድፈርን እንደ ጦርነት ስልት እየተጠቀመች ነው – አምነስቲ
በሰሜን ኢትዮጵያ ለዘጠኝ ወራት በዘለቀው ግጭት የተፈጸሙት የመብት ጥሰቶች የጦር ወንጀሎች ናቸው ሲል የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ባወጣው ሪፓርት ገልጿል። የተፈፀሙት...
በትግራይ ሕጻናት ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል ሲል ዩኒሴፍ አስታወቀ
ተመ የሕጻናት መርጃ ድርጅት በምህጻሩ ዩኒሴፍ በቅርቡ ባወጣው መረጃ በትግራይ ከ700 ሺህ በላይ ሕፃናት ከመኖርያቸው መፈናቀላቸውን አመልክቷል። በትግራይ በሚገኙ የተለያዩ የተፈናቃይ መጠልያ...
ፓለቲከኛ አብረሃ ደስታ ታሰሩ
ፍርድ ቤት የቀረቡት የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለሥልጣን አቶ አብርሐ ደስታ “ግጭት በመቀስቀስ” እና “ሕገ-ወጥ ሽጉጥ ይዞ በመገኘት” መጠርጠራቸውን ጠበቃቸው ተናገሩ። አቶ...
ባለቤቲን ያለምንም ጥፋቱ የቤቱ በር ላይ ገደሉት
የህወሓት ታጣቂዎች በዳባት ወረዳ በጭና በፈጸመው ጭፍጨፋ ከ200 በላይ ንጹሀን ተገድለዋል። ከእነዚህ ንጹሀን መካከል የወይዘሮ ካሳዬ ዘውዱ ባለቤት አንዱ ናቸው። “ባለቤቴን ቤታችን...
የአማራ ልዩ ኃይል ከሽረ እንዳሥላሴ እና አካባቢው መውጣቱ ተገለጸ
በትግራይ ሽረ እንዳሥላሴ እና አካባቢው ተሰማርቶ የነበረው የአማራ ልዩ ኃይል ከአካባቢው እንዲወጣ መደረጉን የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ የኢትዮጵያ...











