በአማራ ተውላጆች ላይ የሚደርስው ሞት ይብቃ በማለት የሰክላ እናቶች አድባባይ ወጡ  

በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ እናቶች በአደባባይ በመውጣት በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደረግውን ዘር ተኮር ጭፍጭፋ ተቃወሙ።  ክስፍራው የደረሰን መረጃ እንድሚያሳየው፤ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ነው እናቶች በመንግስት መር ዘግናኝ ጭፍጭፋ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ሞት ይብቃ በማለት ተቃውሟቸውን ያሰሙት ። ሰልፈኞች አክለውም በኦሮሚያ የመንግስት መዋቅር ውስጥ ተሰግስገው ለዜጎች እልቂት ተጠያቂ የሆኑ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀው፤ የእውነት መንግስት ካለ በክልሉ የዘር ተኮር ጥቃት ሰለባ የሆኑ የአማራ ተወላጆ ከለላ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡ የሰከላ ነዋሪ ቤተሰቦቻቸው መንግስት መንገድ ዘግቶ ማስጭፍጭፉን ያቁም ብለዋል። 

ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ በተፈጠረ ግጭት ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸው መዘገባችን ይታውሳል። ለግጭቱ በአካባቢው የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች የክልሉን ልዩ ኃይልና ኦነግ ሸኔ የተባለውን ታጣቂ ተጠያቂ ሲያደርጉ፣ የኦሮሞ ተወላጆች ደግሞ “ፋኖ” የተባለውን ታጣቂ ይከስሳሉ። 

በከተማዋ የሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች መንግስት ኦነግ ብሎ የሚጠራውና የክልሉ ልዩ ኃይል በንፁሐን ላይ ጥቃት ከፍተው ብዙዎች እንዲሞቱና እንዲፈናቀሉ ምክንያት መሆኑን ተዘግቧል፡፡

የአማራ ተውላጅ ነዋሪዎች ለዲደብሊው እንድተናገሩት “ሸኔና ልዩ ኃይል ተቀላቅሎ ንፁሐን ህዝብ እየጨረሰ ነው ያለው፣ ንብረትም እንዳለ ተዘርፎ ወድሟል፣ ምንም የለም ቤትም እያቃጠሉ ነው፣ ህዝቡም በርግጎ ጫካ ገብቷል፣ ንፁሐንም እለቀ፣ እየሞተ ነው ያለው፣ እኛም ተፈናቅለን ነው ያለነው ወደ ጫካ ወደ በረሀ፣ ደካሞች አሉ፣ ህፃናት አሉ እርጉዞች አሉ፡፡ መጀመሪያ ገበሬውና ኦነጉ ጋር ነበር አሁን፣ ልዩ ኃይል አስጠርተው አጋጠሙት፣ ሬሳም አልተነሳ፣ አሁን ግን ህዝቡ ሬሳ ወድቆ አንቀመጥም ብሎ እየገጠመ ነው፡፡”