የአሜሪካ የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ ልዑክ ጄፍሬይ ፌልትማን ከምክትል ጠቅላይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተወያዩ

የአሜሪካ የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ ልዑክ ጄፍሬይ ፌልትማን ከምክትል ጠቅላይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር አዲስ አበባ ውስጥ መወያየታቸው ተገለጠ። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኩል ስለ ሕዳሴ ግድብ፣ ስለ ኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይ፣ ስለ መጪው ጠቅላላ ምርጫ እና ሌሎች ጉዳዮች ገለፃ እንደተደረገላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዐሳውቋል።

የአሜሪካ የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ ልዑክ ጄፍሬይ ፌልትማን ከምክትል ጠቅላይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር አዲስ አበባ ውስጥ መወያየታቸው ተገለጠ።  በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኩል ስለ ሕዳሴ ግድብ፣ ስለ ኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይ፣ ስለ መጪው ጠቅላላ ምርጫ እና ሌሎች ጉዳዮች ገለፃ እንደተደረገላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ዐሳውቋል።

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላት ግንኙነት ስትራቴጅክና ረጅም ዓመታት ያስቆጠረ መሆኑን ይህንንም ለማጠናከር ጠንካራ ፍላጎት ያላት መሆኑ እንደተገለፀላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል። ልዑኩ የሕዳሴው ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ዲፕሎማሲያዊ በሆነ በሰላማዊ መንገድ እንዲቋጭ፣ ሁሉንም በሚጠቅም ሁኔታ እንዲፈታ ያላቸውን ፍላጎት ገልፀው በአሜሪካ በኩል ተልእኳቸውም ይህን ለማሳካት እንደሆነ ገልፀዋል ብለዋል። በልዑኩ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኩል የተደረገው ውይይት «ገንቢ ነበር» ብለዋል ቃል ዐቀባይ ዲና ሙፍቲ።