በትግራይ ያንዣበበው የረሃብ አደጋ

ከአንድ ሳምንት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው የነበሩት የዩናይትድ ኪንግደም የረሃብ መከላከል ልዩ መልዕክተኛ ኒክ ዳየር ወደ ትግራይ ክልል አቅንተው ነበር።

ልዩ መልዕክተኛው በጦርት ውስጥ ባለችው የትግራይ ክልል የነበራቸውን ቆይታ ሲያጠቃልሉም የተመለከቱትን ሁኔታ “ቀውስ” ሲሉ ጠርተውታል።

ከጉብኝታቸው መልስ በሰጡት አስተያየትም “በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ በፍጥነት እያሽቆለቆለ ነው። የረሃብ አደጋን ለማስቀረት ያለው ብቸኛ መንገድ ጦርነቱን አሁኑኑ ጋብ ማድረግ ነው። በጦርነቱ ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ሁሉም አካላት ለሰብአዊ እርዳታ ሲሉ ተኩስ አቁም ማድረግ አለባቸው” ሲሉ መልክት አስተላልፈዋል።

ኒክ በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት በዚህ መልዕክት የግብርና ሥራዎች እንዲጀመሩ እና በተለይም ገበሬዎች ዘር መዝራት እንዲጀምሩ ግጭቱን ጋብ ማድረግ አንገብጋቢ መሆኑን አክለው ገልፀዋል። ሙሉ ዘገባውን ቢቢሲ ላይ ያንብቡ።