ባለቤቲን ያለምንም ጥፋቱ የቤቱ በር ላይ ገደሉት
የህወሓት ታጣቂዎች በዳባት ወረዳ በጭና በፈጸመው ጭፍጨፋ ከ200 በላይ ንጹሀን ተገድለዋል። ከእነዚህ ንጹሀን መካከል የወይዘሮ ካሳዬ ዘውዱ ባለቤት አንዱ ናቸው። “ባለቤቴን ቤታችን...
በጨለንቆ ከአንድ ቤተሰብ አምስት ሰው ተገደለ
በጨለንቆ ባለፈው ሰኞ በሃገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ቢያንስ 16 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶችም ቆስለዋል። ከተገደሉት ሰዎች አምስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው። ሳሊ ሃሰን ኢብሮና አብዲ...
ባልደራስ ሰልፍ ጠራ
መንግሥት ማንነት ላይ ያተኮሩ ጥቃቶችን ማስቆም አለመቻሉ፣ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የፍትሕ እጦት፣ የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉዳይ እንዲሁም የሱዳን...
የጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ጉዳይ
ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ሚያዚያ 23 አለም አቀፉ የላብ አደሮች ቀን እየተከበረ በዋለበት ዕለት፣ ማለዳ 4 ሰአት ከሚኖርበት አያት ባቡር ጣቢያ አካባቢ ባልታወቁ ...
ጋዜጠኛና መምህር መስከረም ታሰረች
ጋዜጠኛና መምህር መስከረም አበራ ዛሬ ማክሰኞ ታኅሣሥ 04/2015 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋሏን ኢትዮታይምስ አረጋግጣለች። መስከረም...
በትግራይ ያንዣበበው የረሃብ አደጋ
ከአንድ ሳምንት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው የነበሩት የዩናይትድ ኪንግደም የረሃብ መከላከል ልዩ መልዕክተኛ ኒክ ዳየር ወደ ትግራይ ክልል አቅንተው ነበር።
አቶ ልደቱ በቁጥጥር ስር ዋሉ
የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መስራች ልደቱ አያሌው ሐምሌ 17/2012 በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ።
የፓርቲው ፕሬዘዳንት አዳነ ታደሰ በፓርቲው ፌስ...
ፓለቲከኛ አብረሃ ደስታ ታሰሩ
ፍርድ ቤት የቀረቡት የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለሥልጣን አቶ አብርሐ ደስታ “ግጭት በመቀስቀስ” እና “ሕገ-ወጥ ሽጉጥ ይዞ በመገኘት” መጠርጠራቸውን ጠበቃቸው ተናገሩ። አቶ...
በምርመራ ወቅት እስረኞች ላይ የተፈጸሙ አስቃቂ ጉዳቶች
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ የክስ መዝገብ በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ ከተከሰሱት 38 ተከሳሾች መካከል 16 እስረኞች ላይ በምርመራ ወቅት የደረሰባቸውን...
ገደቡ ካልተነሳ የበጀት ድጎማውን እንደማይለቅ የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ
የአውሮፓ ኅብረት የሰብዓዊ ዕርዳታ የሚያቀርቡ ድርጅቶች በትግራይ ክልል ያለ ገደብ እንዲንቀሳቀሱ እስካልተፈቀደ ድረስ፣ ለኢትዮጵያ ያፀደቀው የበጀት ድጎማ እንደማይለቀቅ አስታወቀ።
የኅብረቱ ምክትል ኮሚሽነርና የውጭ ጉዳይና ደኅንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፍ ቦሬል በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ቀውስ መባባስ የአውሮፓ ኅብረትን በእጅጉ እንደሚያሳስበው፣ በዚህ ጉዳይ ላይም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በስልክ መወያየታቸውን ገልጸዋል።
በውይይታቸው ወቅትም በትግራይ ክልል ያለው ሰብዓዊ ቀውስ ኅብረቱን እንደሚያሳስበው ለአቶ ደመቀ እንደገለጹላቸው የጠቆሙት ኃላፊው፣ ሰብዓዊ ዕርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች በትግራይ ክልል ያለ ምንም ገደብ እንዲንቀሳቀሱ ሊፈቀድ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ዓርብ ጥር 7 ቀን 2013 ዓ.ም. አስታውቀዋል።
‹‹ይህ የአውሮፓ ኅብረት ጥያቄ አይደለም፡፡ ይህ በዓለም አቀፍ ሕግ የተደነገገ የመንግሥታት ግዴታ ነው፤›› ሲሉም በትዊተር ገጻቸው አመልክተዋል።












