አሜሪካ የኤርትራ ሠራዊት ከኢትዮጵያ እንዲወጣ ግፊት አደርጋለሁ አለች

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአሜሪካ መንግሥት ወኪል ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ የአፍሪካን ቀጣናዊ ሰላም በሚመለከት ማክሰኞ ግንቦት 10 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ሰላምና ፀጥታ ጉዳይ የፕሬዚዳንት ጆሴፍ ባይደን አስተዳደር ዋና ትኩረት መሆኑን በመጥቀስ በተለይ ከትግራይ ክልል የኤርትራ ሠራዊት ለቅቆ እንዲወጣ ለማድረግ ግፊት ይደረጋል ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ ባለፉት አምስት ወራት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርገው እንደሠሩና ልዩ መልዕክተኛ ሴኔተር ክሪስ ኩንስን ወደ ኢትዮጵያ ልከው ውይይት ማድረጋቸውን በማስታወስ፣ በቅርቡ በኢትዮጵያና በሌሎች የቀጣናው አገሮች ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፊልትማን ከኢትዮጵያ እንደተመለሱ በመጠቆም፣ ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እንደሚሠሩና እንደሚከታተሉ ተናግረዋል፡፡ እሳቸውም ቢሆኑ የኢትዮጵያን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተሉ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

በዚህም አግባብ በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ በተመለከተ ለመንግሥት ሥጋታቸውን ማቅረባቸውን፣ የኤርትራ ሠራዊትም ከኢትዮጵያ እንዲወጣ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ‹‹እንዲህ ባሉ ተግባራትም ከኢትዮጵያ ጋር በንቃት እየሠራን እንገኛለን፤›› ብለዋል፡፡ ሙሉውን ለማንብብ ይህን ይህን ሊንክ ይጫኑ