በአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉት ወገኖች ለረሃብ ተጋለጡ

በክልሉ ከ700 ሺህ በላይ በምግብ ለሥራ የሚተዳደሩ ወገኖች መኖራቸው ተገልጿል። በአማራ ክልል በአጠቃላይ ከአንድ ሚሊዮን 300ሺህ በላይ የዕለት ምግብ ርዳታ የሚፈልጉ ወገኖች እንደሚኖሩ ነው የተገለጸው። 

በአማራ ክልል ህወሓት በተቆጣጠራቸው የምግብ ለሥራ ተጠቃሚ አካባቢዎች ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ፈጥኖ የርዳታ እህል የሚያደርስ ካልሆነ ከፍተኛ የርሀብ አደጋና ተያያዥ ችግሮች ሊከሰቱ እንደሚችሉ በአካባቢዎቹ የሚገኙ ነዋሪዎችና ተፈናቃዮች አመለከቱ። በክልሉ ከ700 ሺህ በላይ በምግብ ለሥራ የሚተዳደሩ ወገኖች መኖራቸው ተገልጿል። በአማራ ክልል በአጠቃላይ ከአንድ ሚሊዮን 300ሺህ በላይ የዕለት ምግብ ርዳታ የሚፈልጉ ወገኖች እንደሚኖሩ ነው የተገለጸው። በተለይም በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ በሰሜን ወሎና ሰሜን ጎንደር አንዳንድ አካባቢዎች አብዛኛው ነዋሪ ሕይወቱን በምግብ ለሥራ የሚመራ መሆኑን ከባሕር ዳር ዓለምነው መኮንን ያለከው ዜና ያመለክታል።  (ዲ ደብሊው)