1- ልሙጥ ባንዲራ ስለተያዘ ብቻ ህገመንግስቱ ባህርዳር ላይ ተጥሷል ብለን አርባምንጭ ቦንጋ ወይ ወልቂጤ ላይ ሲሆን ዝም ካልን ባንዲራ ሽፋን ነው፤ አስቀድሞ የተጀመረው የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ አካል ነው ማለት ነው።
2- የዘር ፍሬአቸው ላይ ውሀ የተሞላ የሀይላንድ ኮዳ ተንጠልጥሎ ለወራት የተገረፉ ሲጋራ ላያቸው ላይ ሲተረኮስባቸው የነበሩ ወገኖችን የስቃይ ታሪክ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ህዝቡ የወደደውን ባንዲራ ለምን ያዘ ብሎ መንጣጣት ስብዓዊ አስተሳሰብም የህግ የበላይነት አስተሳሰብም የጎደለው አረመኔነት ነው።
3- ህዝቡ ልሙጥ ባንዲራ መያዙ የሚጥሰው የሠንደቅአላማ አዋጁን እንጂ ህገመንግስቱን አይደለም። የትም ሀገር ሰንደቅአላማ አዋጅ ላይ የሌለ ሲቪል ፍላግን መያዝ የሚከለክል አንቀጽ በአዋጁ መካተቱ ነው የችግሩ መንስዔ። አዋጁ ሊያስገድድ የሚችለው በመንግስት ተቋማት፣ ኤምባሲዎችና በኦፊሴል ኢትዮጵያን ወክለው በተለያዩ አለምአቀፍ መድረኮች የሚውለበለበውን ሠንደቅ አላማ እንጂ ህብረተሰቡ የሚይዘውንና መያዝ የሌለበትን ማስገደድ አይችልም። የባህር ነዋሪ ስቴዲየም ይዞ መሄድ ያለበትን ልምረጥልህ የሚል አዋጅ ኢትዮጵያ ውስጥ ካልሆነ የትም የለም። ህገመንግስቱ አልተጣሰም። ህገመንግስቱ ግለሰቦች የፈለጉትን ባንዲራ መያዝ አይከለክልም። በማናውቀው ነገር አንመጻደቅ።
(አዲስ ቸኮል)