የሕወሓት ኃይሎች በአማራ ክልል ወረራ ፈፅመውባቸው በነበሩ አካባቢዎች እስካሁን ባለ መረጃ ከ147 በላይ ሴቶችን መድፈራቸውን የክልሉ መንግስት ዐስታውቋል። የተደራጀና ወጥ ጥናት ከተካሄደ ቁጥሩ በጣም ከፍተኛ እንደሚሆን ደግሞ አንድ ሰብአዊ መብት ተሟጋች ኅብረት ገልጧል።
የሕወሓት ኃይሎች በአማራ ክልል ወረራ ፈፅመውባቸው በነበሩ አካባቢዎች እስካሁን ባለ መረጃ ከ147 በላይ ሴቶችን መድፈራቸውን የክልሉ መንግስት ዐስታውቋል። የተደራጀና ወጥ ጥናት ከተካሄደ ቁጥሩ በጣም ከፍተኛ እንደሚሆን ደግሞ አንድ ሰብአዊ መብት ተሟጋች ኅብረት ገልጧል። በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቀት በመቃወም ነገ በአማራ ክልል ደረጃ ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳልም ተብሏል።
የሕወሓት ኃይሎች ባለፉት 6 ወራት በአማራ ክልል ወረራ በፈፀመበት ወቅት በሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ቢያደርስም የሴቶች ጥቃት ግን ከፍተኛው እንደነበር የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ዐስታውቋል። የጽ/ቤቱ ኃላፊዋ ወ/ሮ አስናቁ ድረስ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ወራሪ ያሉት ኃይል ህፃናትና አዛውንቶችን ያለጧሪ አስቀርቷል አካል ጉዳተኞችን አንገላትቷል።
እስካሁን ባለው መረጃ ከ147 በላይ ህፃናትንና አዛውንቶችን ጨምሮ በርካቶችን ደፍሯል ብለዋል፡። የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ የሺሐረግ ፋንታሁን በበኩላቸው ቡድኑ በአማራ ክልል በቆየበት ወቅት እድሜ ሳይለይ በሁሉም ላይ ትቃት ፈፅሟል ነው ያሉት። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ድርጅቶች ኅብረት ዋና ዳይሬክተር አቶ መሱእድ ገበየሁ ሕወሓት በአማራ ክልል በቆየባቸው አካባቢዎች ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈፀሙን አረጋግጠዋል፡፡