የአማራ ልዩ ኃይል ከሽረ እንዳሥላሴ እና አካባቢው መውጣቱ ተገለጸ

በትግራይ ሽረ እንዳሥላሴ እና አካባቢው ተሰማርቶ የነበረው የአማራ ልዩ ኃይል ከአካባቢው እንዲወጣ መደረጉን የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት ጦርነቱን ለማስቆም በደረሱት የሰላም ስምምነት መሠረት የአማራ ልዩ ኃይሎች ከአካባቢው እንዲወጣ ተደርጓል ብሏል። 

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የመከላከያ ሚኒስቴር ትናንት ሐሙስ ጥር 04/2015 ዓ.ም. በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ነው ልዩ ኃይሉ መውጣቱን የገለጸው።

“የኢትዮጵያ መንግሥት በሽረ እና አካባቢው ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር ተሠልፎ አገራዊ ተልዕኮን ሲፈፅም የነበረው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል በስምምነቱ መሠረት ከቀጠናው እንዲወጣ አድርጓል” ብሏል። (ምንጭ ቢቢሲ)