የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንትና ምክትላቸው በፈቀዳቸው ለቀቁ

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትላቸው በፍቃዳቸው ከስራቸው መልቀቃቸው ታወቀ። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊ እና ምክትል ፕሬዝዳንት ሰለሞን አረዳ በገዛ ፍቃዳቸው ከኃላፊነት መልቀቃቸውም ተገልጿል። በምትካቸውም የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበለትን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንትን ሹመት አጽድቋል።

ምክር ቤቱ አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት ከበደን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አድርጎ በ3 ድምፀ-ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ሹመታቸውን አጽድቋል።

በተመሳሳይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ወይዘሮ አበባ እምቢአለን ሹመት በሙሉ ድምፅ ያፀደቀ ሲሆን፤ ተሿሚዎችም በጉባኤው ፊት ቀርበው ቃለ-መሐላ ፈፅመዋል።