እውቁ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ በፓሊስ ተይዞ መወሰዱን ምንጮች አስታወቁ። የቀድሞው የአዲስ ነገር ጋዜጣ ባልደረባ እንዲሁም ከስደት መልስ ተራራ ኔትወርክ የተሰኘው የኦንላይን ሚዲያ መስራችና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ከመኖሪያ ቤቱ በፀጥታ ኃይሎች ታፍኖ መወሰዱን መምንጮች አረጋግጠዋል። ሲቪል የለበሱ እና ፖሊስ ነን ያሉ ግለሰቦች እንዲሁም መሳሪያ የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት ጋዜጠኛ ታምራትን ለጥያቄ ትፈለጋለህ በማለት ዛሬ ታህሳስ 01/2014 ረፋድ ላይ አፍነው እንደወሰዱት ለማወቅ ችለናል።
የፌደራል ፓሊስ አባላቱ ምንም አይነት የፍርድቤት የመጥሪያ ወረቅት እንዳላቀረቡና ከመኖሪያ ቤቱ በርካታ የሚዲያ ስራው ጋር የተገናኙ ንብረቶችን በተደጋጋሚ በመበርበር እንደወሰዱ ታውቋል። ፓሊስ ጋዜጠኛው የተጠረጠረበትን ወንጅል ለመናገር ፈቃደኛ እንዳልነበረ ያገኛናቸው መረጃዎች ያሳያሉ፤ በደፈናው ለጥያቄ ነው የምንፈልገው ከማለት ውጪ።
ጋዜጠኛ ታምራት በጋዜጠኝነት ሙያው ምክኒያት ከአመታት ስደት በኃላ በለውጡ ተበረታተው ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ጋዜጠኞች መካከል አንዱ ነው። ይሁንና የጠ/ሚ አብይ አስተዳደር በመንግስትና ብሄርን መሰረት ያደረገው ህገመንግሱትን የሚቃወሙ ጋዜጠኞችን፤ የማህበራዊ አንቂዎችንና ፓለቲከኞችን እንደሚያሳድድና እደሚሸማቅቅ መረጃዎች ያሳያሉ። ጋዜጠኛ ታምራትም በተለይም ለዜግች ግጭት እንዲሁም ህይወት መጥፋታ ምክኒያት የሆነውን ብሄርን ማእከል ያደረገውን ህገመንግስት በመተቸት ይታወቃል። ጋዜጠኛ ታምራትም ይህ የመናገር መብቱን በመጠቀም በብሄር ተኮር ህገመንግስቱ ላይ የሚሰነዝረው የሰላ ትችት ለእስር ሳይዳርገው እንዳልቀረ ይገመታል። የጋዜጠኛ ታምራት እስር የጠ/ሚ አስተዳደር ከጊዜ ወደ ጊዜ በዜጎች ላይ የሚያደርሰውን የመናገር መብት ጭፍለቃ አጠናክሮ መቀጠሉን የሚያመላክት ነው።