በቅርቡ በአፋር ክልል አዲስ ዉጊያ መቀስቀሱን ዩናይትድ ስቴትስ ተቃወመች።የአፋር ክልልና የኢትዮጵያ የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ከፈተዉ ባሉት ጥቃት በርካታ ሰዉ ተገድሏል።በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ተፈናቅሏል። የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ትንናት ለጋዜጠኞች እንደገሩት ዉጊያዉ በቀጥታ ከሚያደርሰዉ ጥፋት በተጨማሪ የሰብአዊ ዕርዳታ አቅርቦትንም ስለሚያዉክ ባስቸኳይ መቆም አለበት።በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት የዛሬ 3 ወር ግድም የጣለዉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማንሳት የጀመረዉን እርምጃ ቃል አቀባዩ አድንቀዋል። (ዲ.ደብሊው)