የውጭ አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ ብድር ለመልቀቅ እያመነቱ ነው ተባለ

ለኢትዮጵያ ዋነኛ አበዳሪ የሚባሉ የፋይናንስ ተቋማት ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ብድር ለመልቀቅ እያቅማሙ ነው።

ይህም የሆነበት ዋነኛው ምክንያት ተጨማሪ ብድር ለአገሪቱ መስጠት የመክፈል አቅሟን የበለጠ ሊያዳክም ይችላል ከሚል ስጋት ነው።

በገንዘብ ሚኒስትር አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሮይተርስ እንደተናገሩት ለምሳሌ የቻይናው ኤክዚም ባንክ እሰጣለው ብሎ የነበረውን ከፍተኛ ገንዘብ ለመልቀቅ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።

ይህም ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የቻይናው ኤክዚም ባንክ ለኢትዮጵያ ከመስጠት የታቀበው የብድር መጠን 339 ሚሊዮን ዶላር ነው። ይህን ያሉት የገንዘብ ሚኒስቴር የቻይና ትብብር ዳይሬክተር ደምሱ ለማ ናቸው።

ነገር ግን የቻይናው ኤክዚም ባንክ ለኢትዮጵያ ብድር ለመልቀቅ በማቅማማት ላይ ያለ ብቸኛው የፋይናንስ ተቋም አይደለም። ሙሉውን ቢቢሲ ላይ ያንብቡ