ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጡ ወጣቶች በገፍ የምርጫ ካርድ እየተሰጠ ነው – ባልደራስ

በአዲስ አበባ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያ 17 ላይ ከአዲስ አበባ ውጭ በገፍ ለመጡ ወጣቶች በሕገ ወጥ ሂደት የመራጮች ካርድ እየታደለ መሆኑን የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የምርጫ ጣቢያዎች የክትትል ቡድን አስታውቋል።

ክስተቱን በምስል ለመቅረፅ የሞከሩት የባልደራስ የአካባቢው ተወካይ አቶ አንተነህ ደሳለኝ በፖሊስ ታስረዋል።

ወጣቶቹ የመጡት ኮድ 3፡27401 ኦሮሚያ በሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ተሳፍረው ነው። የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 4፡03548 የሆነ ፒካፕ የመንግሥት ተሽከርካሪ ደግሞ አይሱዙውን እያጀበ የምርጫ ጣቢያው ድረስ አድርሷቸዋል

የአካባቢው ኗሪዎች ወጣቶችን እንደማያውቋቸውና እንግዳ እንደሆኑም ተናግረዋል። ሙሉውን መረጃ ላይ ያንብቡ።