ዶናልድ ቡዝና ም/ጠሚ ደመቀ ተወያዩ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሱዳንና ደቡብ ሱዳን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ የተመራ ከፍተኛ ልዑካንን ዛሬ በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።አቶ ደመቀ ለልዑካን ቡድኑ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድርና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች አስመልክተው ገለጻ አድርገውላቸዋል:: ኢትዮጵያ ለአባይ ወንዝ 86% ውሃ የምታበረክት አገር መሆኗዋንና 60% የሚሆኑ ዜጎችዋ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ባለማግኘት በጨለማ ውስጥ የሚኖሩ መሆኑን አስረድተዋል።በመሆኑም ግድቡ በጨለማ የሚኖር ህዝቧን ብርሃን እንዲያገኝ ለማድረግ የታለመ ፕሮጄክት መሆኑን ገልጸውላቸዋል።የአባይ ውሃን በፍትሃዊና እኩልነት መርህ ለልማት ማዋል የኢትዮጵያ ህጋዊና ሉዓላዊ መብት መሆኑን አስረድተው፣ ኢትዮጵያ ታችኞቹን የአባይ ተፋሰስ አገራትን የመጉዳትምንም ፍላጎት እንደሌላት አቶ ደመቀ ለቡድኑ ገልፀውላቸዋል።