ባልደራስ ሰልፍ ጠራ

መንግሥት ማንነት ላይ ያተኮሩ ጥቃቶችን ማስቆም  አለመቻሉ፣ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የፍትሕ እጦት፣ የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉዳይ እንዲሁም የሱዳን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት መጣስ ላይ ታይቷል ያለው ቸልታ ሰልፍ ለመጥራት እንደገፋው ፓርቲው አሳውቋል።


ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በአጭር መጠሪያው ባልደራስ  ዋና ዋና ባላቸው አራት ጉዳዮች ላይ ተቃውሞ ለማሰማት ለጥር ዘጠኝ ቀን 2013 ሠላማዊ ሰልፍ መጥራቱን አስታወቀ። መንግሥት ማንነት ላይ ያተኮሩ ጥቃቶችን ማስቆም  አለመቻሉ፣ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የፍትሕ እጦት፣ የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉዳይ እንዲሁም የሱዳን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት መጣስ ላይ ታይቷል ያለው ቸልታ ሰልፍ ለመጥራት እንደገፋው ፓርቲው አሳውቋል። ሰልፉ በአዲስ አበባ ይካሄዳል ያለው ፓርቲው፣ በሌሎች ከተሞች ስለመካሄድ አለመካሄዱ ተቋቁሟል የተባለው ግብረ ኃይል ያሳውቃል ብሏል።ስለጉዳዩ የፓርቲውን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ያነጋገረው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።