ጋዜጠኛና መምህር መስከረም ታሰረች

ጋዜጠኛና መምህር መስከረም አበራ ዛሬ ማክሰኞ ታኅሣሥ 04/2015 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋሏን ኢትዮታይምስ አረጋግጣለች። መስከረም በመንግስት የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመተችት እንዲሁም የሰላ የፓለቲካ ትንታኔ በመስጠት ትታውቃለች። ከምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳያው፤ መስከረም በቁጥጥር ስር የዋለችው ዛሬ ከሰአት  አዲስ አባባ ከመኖሪያ ቤቷ የፓሊስ የደንብ ልብስ በመበሱ ግለሰቦች ነው። ፓሊስ መስከረምን ከጨቅላ ልጇ ነጥሎ እንደወሰዳት ለማወቅ ችለናል። 

መስከረም በፓሊስ ቁጥጥር ስር ስትውል ይህ የመጀመሪያ አይደለም። ግምቦት ወር ላይም በተመሳሳይ ሁኔታ በቁጥጥር ስር መዋሏንና የጋዜጠኞች የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞች የመናግር መብታችውን ከመገድብ እንዲያቆም የታስሩ ጋዜጠኞችንም እንዲፈታ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።  መንግስት በአግዛዙ ላይ የሰላ ትችት የሚያደርጉ ጋዜጦችን በማሸማቀቅ እንዲሁም የሰብአዊ ጥሰት እንደሚያደርስ ሲፒጄ በተለያዩ ሪፓርቶች አጽኖት ሰጥቶ መተቸቱ ይታወቃል።

ዘግይቶ በደረሰን ዜና መሰረት የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ መንግስት መስከረም አበራን እንዲፈታ የሚጠይቅ መግለጫ በድረ ግጹ አውጥቷል።

ጋዜጠኛ መስከረም ኢትዮን ንቃት የተሰኘውን የራሷን ኦንላይን ሚዲያ ከመመስረቷ በፊት ለኢትዮታይምስ የፓለቲካ ትንታኔና መጣጥፍ በማሰናዳት ትሳተፍ ነበር።

መንግስት በተለይም መንግስትንና የኦሮሚያ ክልል የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ የሚያደርሰውን ጭቆና የሚቃወሙ ልሂቃንና ጋዜጦኞችን ማሳደዱን መቀጠሉን ታዛቢዎች ይናግራሉ።