በሰሜን ኢትዮጵያ ለዘጠኝ ወራት በዘለቀው ግጭት የተፈጸሙት የመብት ጥሰቶች የጦር ወንጀሎች ናቸው ሲል የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ባወጣው ሪፓርት ገልጿል። የተፈፀሙት የፆታ ጥቃት ወንጀሎች ክብደት እና መጠን በጣም አስደንጋጭ፣ የጦር ወንጀል ናቸው በማለት ጥቃቱ እንዲቆም ጠይቋል። ድርጅቱ ሪፓርቱን ይፋ ያደረገው 63 የጾታዊ ጥቃት ተጠቂዎችን በማነጋግር ምርምራ ካካሄደ በሃላ እንደሆነ በሪፓርቱ ጠቁሟል።
ከጾታዊ ጥቃት ሰለባዎች መካከል አስራ ሁለቱ ወታደሮችና ሚሊሻዎቹ ከቤተሰብ ህጻናትን ጨምሮ በቤተሰብ አባላት ፊት እንደደፈሯቸው ተናግረዋል። አምስቱ በወቅቱ ነፍሰ ጡር ነበሩ እንደነበሩ ሪፓርቱ አትቷል።
በዚህ አስከፊ የሰብአዊ ቀውስ ተጠቂዎች መከካከል አንድ እናት በሴት በልጆቿ ፊት በቡድን በመንግስት ወታደሮች መደፈሯል ያትታል። የመብት ተሟጋች ድርጅቱ በኢትዮጵያ ወታደሮች፣ በኤርትራ አጋሮቻቸው ወይም ከአጎራባች ክልል በመጡ የመንግስት ደጋፊ ታጣቂዎች መደፈራቸውን በሪፓርቱ ጠቁሟል። በተያያዘ አስገድዶ መድፈር የደረሰባቸው ከ 8 እስከ 72 አመት የእድሜ ክልል የሚገኙ እንደሆነ ደህንነቷን ለመጠበቅ ስሟን መጥቀስ ያልቻለች ነገር ግን በክልሉ ውስጥ የምትሰራ ለጋርዲያን ተናግራለቸ።
አስግድዶ መደፈር ከደረሰባቸው መካከል፤ የ35 አመቷ እናት “ሦስቱ ልጄ ፊት ለፊት ደፈሩኝ። ከእኛ ጋር አንዲት የስምንት ወር ነፍሰ ጡር ሴት ነበረች፣ እርሷንም ደፈሯት” ስትል ተናግራለች።
ሌላ እናት ደግሞ ከሁለት ልጆቿ ጋር ስትጓዝ በኤርትራ ወታደሮች መያዟን ተናግራለች። “ከመካከላቸው አምስቱ በልጆቼ ፊት ደፈሩኝ። … ከዚያም መንገድ ላይ ጥለውኝ ሄዱ” ስትል መናገሮኗን ሪፓርቱ ጠቁሟል። አምነስቲ ያነጋገራቸው አንዳንድ ሴቶች ለሳምንታት ሲታሰሩ እና በተደጋጋሚ እንደተደፈሩ፣ ብዙ ጊዜ በበርካታ ወንዶች እንደተደፈሩ ተናግረዋል።
የምነስቲን ሪፓርት ተከትሎም በአውሮፓ ፓርላማ የሴቶች መብት ተሟጋች ኮሚቴ ኃላፊ ኤቭሊን ሬነር በትግራይ ለተፈጸመው ሰፊ የፆታዊ ጥቃት ጥቃት ወንጀለኞች እንዲጠየቁ ጠይቀዋል። አሁንም ከቦስኒያና ከሩዋንዳ ትምህርት አልተውሰደም በማለት ኮንናለች።
የኢትዮጵያ መንግስት ሪፖርቱ “የተበላሸ የአሰራር ዘዴ” ላይ የተመሰረተ ነው ብሏል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምነስቲ በኢትዮጵያ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻዎችን ፈጽሟል ሲል ይከሳል። ኢትዮጵያ በማንኛውም ሁኔታ ጾታዊ ጥቃትን ታወግዛለች በማለት የአምነስቲን ሪፓርት አጣጥሎታል።
አምነስቲ በበኩሉ ግጭቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ መሰል ጥቃቶች መስፋፋቱን የሚያሳዩ “አሳማኝ ማስረጃዎች አሉኝ” ብሏል።