የነጃዋር ታዳሚዎች ላይ ፍርድቤቶ የአልባሳት መልክት እገዳ ጣለ

ፍርድ ቤቱ በእነጃዋር መሃመድ የችሎት ሂደት ላይ ድጋፍንም ሆነ ተቃውሞን የሚያመላክቱ አልባሳትን ለብሶ ችሎት መታደምን ከለከለ፡፡ተጠርጣሪዎቹ ከዚህ በፊት በነበረ ቀጠሮ ላይ ቤተሰቦቻችን በለበሱት ልብስ በችሎት ካልታደሙ የእምነት ክህደት ቃላችን አንሰጥም ሲሉ ተከራክረው ነበር፡፡

ፍርድ ቤቱም ይህን መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ የያዘ ሲሆን፥ በዛሬው እለትም ማንኛውም በችሎት የሚታደም አካል አድማ የሚመስሉ ድጋፍንም ሆነ ተቃውሞን የሚያመላክቱ አልባሳትን ለብሶ ችሎት መታደም እንደማይችል ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

በተጨማሪም ችሎቱ ገለልተኛ እና ነፃ ሆኖ የሚዳኝበት እንደመሆኑ እንደዚህ አይነት አልባሳትን ለብሶ መግባት አይቻልም ሲልም ክልከላ ጥሏል፡፡ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች የወንጀል ችሎትም፥ የተጠርጣሪዎቹን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ለየካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡(ኤፍ ቢ ሲ)