አቶ ልደቱ በቁጥጥር ስር ዋሉ

የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መስራች ልደቱ አያሌው ሐምሌ 17/2012 በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ።


የፓርቲው ፕሬዘዳንት አዳነ ታደሰ በፓርቲው ፌስ ቡክ ገጽ ላይ እንዳሰፈሩት መጥሪያ የያዙ ፖሊሶች ልደቱን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በቁጥጥር ስር እንዳዋሉት በስልክ ደውለው እንደነገራቸው እና በመጥሪያውም ላይ በቢሾፍቱ ከተማ የተቀሰቀሰውን ቀውስ አስተባብረሀ፣ በገንዘብ ደግፈሀል በሚል ጥርጣሬ እንደሆነ አስታውቋል።
ፖለቲከኛው በፌደራል ፖሊስ ከአዲስ አበባ ከተማ ተይዘው ወደ ቢሾፍቱ መወሰዳቸውንም ፕሬዘዳንቱ ጨምረው ገልጸዋል። ልደቱ አያሌው ከሳምንታት በፊት ይኖሩበት በነበረው ቢሾፍቱ ከተማ በድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በተቀሰቀሰው ግርግር ለደኅንነትዎት በሚል በኦሮሚያ ፖሊስ አጃቢነት ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ መደረጋቸውም ተገልጿል።


ሸገር ራዲዮ እንደዘገበው በተንቀሳቃሽ ስልካቸው መደወላቸውን እና ልደቱ አያሌው በራሳቸው አንደበት በቁጥጥ ስር ውለው ለኦሮሚያ ፖሊስ አስተላልፎ ሊሰጣቸው እንደሆነም መናገራቸው ታውቋል። ከሰሞኑ በድምጻዊው ግድያ ጋር በተገናኘ በርካታ በኦሮሚያ ክልል ከተሞች አለመረጋጋቶች እና ኹከቶች መከሰታቸው የተከሰቱ ሲሆን ከክልል ከተሞች ውስጥም አንዱ የቢሾፍቱ ከተማ መሆኑ የሚታወስ ነው።