አዲስ አበባ የተጀመረው የጅምላ አፈሳ እንዲቆም ተጠየቀ ፤ አክቲቭስቶች ዘመቻ እንጀምራለን ብለዋል።ለቡራዩ ተፈናቃዮች እርዳታ ለማድረስ የሚሄዱ የአዲስ
አበባ ወጣቶችን ማፈሱ የሕዝብን ቁጣ ቀስቅሷል። በቡራዩ አከባቢ በጽንፈኛና ዘረኛ ሃይሎች የተደረገውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ወንጀለኞችን ከማሳደድ ይልቅ ንፁሃን ሃገርና ወገን ወዳዶችን ማሳደዱ ሊቆም ይገባል ሲሉ የ አዲስ አበባ ነዋሪዎች ድምጻቸውን ያሰሙ ሲሆን የታሰሩት እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
የታሰሩት ካልተፈቱ በማሕበራዊ ድረገጽ ዘመቻ ይጀመራል ያሉት ደግሞ ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ የሆነ አክቲቭስቶችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ናቸው። የመብት ተሟጋቾች በንጹሃን ላይ የሚደርሰ የጅምላ እስር እንዲቆምና የታሰሩት ተፈትተው በሃገሪቱ እኩልነትና የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን ጠይቀዋል። ሃገሪቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኗንና ሰርዓት አልበኝነት መስፈኑንም በርካቶች ይናገራል።