በምርመራ ወቅት እስረኞች ላይ የተፈጸሙ አስቃቂ ጉዳቶች

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ የክስ መዝገብ በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ ከተከሰሱት 38 ተከሳሾች መካከል 16 እስረኞች ላይ በምርመራ ወቅት የደረሰባቸውን ጉዳት በሪፖርቱ አኳትቷል። በዚህም መሰረት:-

1) ከበደ ጨመዳ:_ ቀኝ እጅ ላይ ትንሽ ጠባሳ፣ ቀኝ እግር አውራ ጣት ስብራት፣
2)ኢብራሂም ካሚል:_ ቀኝ እግር ላይ ጠባሳ፣ ግራ እጅ ላይ ጠባሳ፣ የካቴና እስር ምልክቶች፣
3) አግባው ሰጠኝ:_ ግራ ታፋ ላይ ሰፊ ጠባሳ፣ ቀኝ እግር ላይ ጠባሳ፣ ግራ እግር ላይ በሚስማር የተመታ ምልክት፣ ጀርባ ላይ የግርፋት የሚመስሉ ምልክቶች፣
4)ቶፊቅ ሽኩር:_ ቀኝ እጅ ላይ ጠባሳ፣ የሁለት እግር አውራ ጣት ጥፍር መነሳት፣ ግራ እጅ ጠባሳ፣
5) ሸምሱ ሰይድ: _የጀርባ የግርፋት የሚመስሉ ምልክቶች፣
6) ሚስባህ ከድር:_ የካቴና የእስር ምልክቶች፣ ቀኝ እጅ ላይ ሰፊ ጠባሳ፣ ግራ እጅ ላይ አነስተኛ ጠባሳ፣ ቀኝ እና ግራ ታፋ ላይ ጠባሰ፣ የግራ እጅ ጠቋሚ ጣት ስብራት፣
7) ፍፁም ጌታቸው: _ የቀኝ እጅ ጉዳት፣
8) ተመስገን ማርቆስ:_ የቀኝ እጅ ስብራትና ጠባሳ፣ ሁለቱም እግሮች ሰፋፊ ጠባሳዎች፣
9) አሸናፊ መለሰ:_ የቀኝ እና ግራ ታፋ ላይ ጠባሳዎች፣ የግራ እጅ የቀለበት ጣት ስብራት፣
10) ካሳ መሃመድ:_ቀኝ እጅ ጥልቅ ጠባሳ፣ ጭንቅላት ላይ የመፈንከት ምልክት፣
11) ሲሳይ ባቱ:_ ቀኝ እጅ ላይ ጠባሳና የጠቆረ ምልክት፣
12) አቡዱልደፋር አስራት: _ቀኝ እና ግራ እግር አውራ ጣት ጥፍር መነቀል፣
13) ደረጀ መርጋ: _ግራ እግር ላይ ስድስት ጠባሳዎች፣ ሁለቱም እግር ላይ ካቴና እስር የጠቆሩ ምልክቶች፣
14) ቶፊክ ፈርሃ: _ግራ እጅ ላይ ጠባሳ፣ የካቴና እስር የጠቆሩ ምልክቶች፣
15) ኡመር ሀሰን:_ የግራ እግር አውራ ጣትና የቀኝ እግር ከአውራ ጣት ቀጥሎ ያለው ጣት ጥፍር መነቀል፣
16) ሰይፈ ግርማ: _ከጀርባ ትክሻ በግራ በኩል በሚስማር የተመታ ጠባሳ፣ ሁለቱም እግሮች ላይ ጠባሳ፣