የሰላማዊ ዜጎች ደህንነት በትግራይ እንዲጠበቅ አምነስቲ አሳሰበ

የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት እና   የህወሓት ኃይሎች እያደረጉ ባለው ጦርነት  ጦርነት የሰላማዊ ሰዎች ደህንነት ሊጠብቁ እንደሚገባ ዓለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል አሳሰበ። ሁለቱም ኃይሎች ከልክ ያለፈ ኃይል የሚጠቀሙ ከሆኑ  በጦር ወንጀለኝነት ሊያስጠይቃቸው  እንደሚችል በአምንስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል።

የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት እና   የህወሓት ኃይሎች እያደረጉ ባለው ጦርነት  ጦርነት የሰላማዊ ሰዎች ደህንነት ሊጠብቁ እንደሚገባ ዓለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል አሳሰበ። አምንስቲ ትናንት ባወጣው መግለጫው እንዳመለከተው በሁለቱ ወገኖች መካከል እየተደረገ ያለው ጦርነት መቀሌ ከተማ መጠጋቱን ተከትሎ የሰላማዊ ሰዎች ደህንነት ከምንግዜውም በላይ እንደሚያሳስበው አስታውቋል። ሁለቱም ኃይሎች ከልክ ያለፈ ኃይል የሚጠቀሙ ከሆኑ  በጦር ወንጀለኝነት ሊያስጠይቃቸው  እንደሚችል በአምንስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች አጥኚ አቶ ፍሰሃ ተክሌ ተናግረዋል።