ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፡ በመተከል ዞን ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ

%0A%0A https://www.ethiotimes.net/?p=635">
WhatsApp
">
Linkedin
">
ReddIt
">
Telegram

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች በተፈጠረ አለመረጋጋት የፀጥታ ኃይሎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የሆስፒታል ምንጮች ለቢቢሲ ተናገሩ።

ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የህክምና ባለሙያ ለቢቢሲ እንዳስታወቁት በሚሠሩበት ቡለን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ትናንት ምሽት ከአንድ ሰዓት በኋላ ጉዳት የደረሰባቸው የመከላከያ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የልዩ ሃይል አባላት የህክምና ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

ትናንት ህክምና የተደረገላቸው ከትናንት ወዲያ ጉዳት የደረሰባቸው የጸጥታ ኃይል አባላት መሆናቸውንም ጨምረው አስታውቀዋል።

የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያው አክለውም በሆስፒታላቸው ሁለት የመከላከያ አባላት ህይወታቸው አልፎ አስከሬናቸውን መመልከታቸውንም ጨምረው ተናግረዋል።

እንደባለሙያው ከሆነ የተለያየ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታሉ የመጡት የጸጥታ ኃይል አባላት ስምንት ሲሆኑ አምስቱ የመከላከያ ሠራዊት፣ ሦስቱ ደግሞ የልዩ ኃይል አባላት ናቸው።

የጸጥታ አካላቱ ህክምና ከተደረገላቸው በኋላ የመከላከያ ሠራዊት አባላቱ ወደ ባህር ዳር የመከላከያ ሠራዊት ሆስፒታል የክልሉ የልዩ ኃይል አባላት ደግሞ ወደ ፓዊ ሆስፒታል መላካቸውን ጨምረው አስረድተዋል። ለበለጠ መረጃ ቢቢሲን ይጎብኙ